በኑሮ ውድነት የምትታመሰው ደቡብ አፍሪካዊቷ ሀገር ማላዊ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሔድ ጀመረች።

በሀገሪቷ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ወቅት ማላዊያን የሀገራቸውን ቀጣይ ፕሬዚዳንት እና የፓርላማ ተመራጮችን ለማወቅ ድምፅ እየሰጡ ነዉ፡፡

ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን እየተፎካከሩ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም በስልጣን ላይ የነበሩት ፒተር ሙባረክ ዋና ተቀናቃኛቸው ይሆናሉ ተብሏል።

በከተሞች አካባቢ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት የምርጫ ቅስቀሳዉ የተቀዛቀዘ መሆኑን እና የነዳጅ ማደያዎች ውስጥም ረጅም ሰልፎች መከሰታቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ሌላዉ ለመራጮች አሳሳቢ የሆነዉ ጉዳይ ተብሎ የተገለጸዉ በሀገሪቷ ያለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት መሆኑም ተነስቷል፡፡

ሀገሪቷን በፕሬዝዳንትነት ለመምራትም 17 እጩዎች የሚወዳደሩ ሲሆን፤ 7.2 ሚሊየን የተመዘገቡ መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።

ሀና ሰይፉ

መስከረም 6/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *