ከሰሞኑን የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በተለያዩ አካላት እና መገናኛ ብዙሀን የተነሳው ውዝግብ ግድብ በመጠናቀቁ የመጣ እንጂ ሌላ አይደለም ብለውታል፡፡
ግድቡ በመጠናቀቁ ሚናውን የተወጣው ህዝብ እንጂ አንድ አካል ወይንም መንግስት አይደለም ያሉት ዶ/ር ዐብይ ይህንን ተከትሎ ማን በዋናነት ሚናውን ተወጣ ማንስ ነው ከፍኛውን ድርሻ የወሰደው እያሉ መወዛገብ አይገባም የግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ዋነኛ ተዋናይ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡
የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ሚናው የሚገለፀው በአንድ መንግስት ሳይሆን በሁሉም ኢትዮጲያዊ ድርሻ እና ባለቤትነት ጭምር መሆኑንም አክለዋል፡፡
ለታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኔ ሚና ጥቂት(ኢመንት) ናት ያሉት ጠ/ሚ ዐብይ ድሉ የህዝብ ፤ግድብ ደግሞ የጋራ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ከዚህም ባሻገር ግድቡ ከኢትዮጲያ አልፎ የኢትዮጲያ ወዳጆችም ጭምር ነው ሲሉ በጉዳዩን ላይ አስተያየት ሰተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ይህንን ያነሱት የመደመር መንግስት የተሰኘውን አራተኛ መፅሀፍ በትናትናው እለት ሲያስመርቁ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
ቁጭትን መነሻ አድርጎ የመደመር መንግስት የአመራር ሂደት ላይ የሚያጠነጥነው ይህ መፅሀፍ ዛሬ ላይ ሆኖ ነገር ለማየት ነገ ላይ ሆኖ ዛሬን በማየት የተሻለ አለም ለመፍጠር የሚያሰችሉ እይታዎችን ለማመላከት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
ለኢትዮጲያ ትክክለኛ መዳኛ መደመር ነው ያሉት ዶ/ር አብይ አህመድ መፅሀፉን በማንበብ ሃሳብ መስጠት ግምገማ ማድረግ ፤ መሞገት፤ የተሻለ ወይንም የተለየ ልምከታን በመፃፉ ላይ ማድረግ እንደሚቻልበት አስታውቀዋል፡፡
የውልሰው ገዝሙ
መስከረም 7/2017 ዓ.ም
