ኢትዮጲያ የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና ትቀጥል የሚል ኢትዮጲያዊ ከመኖርነት የተገለለ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

በቀይ ባህር ኢትዮጲያን ባለቤት የማድረግ ጉዳይ የግድ መሆኑንም ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ኢትዮጲያ ህጋዊ በሆነ መንገድ የባህር በር አማራጭ እንዴት ታግኝ በሚሉ ሃሳቦች ዙሪያ ላለፉት አምስት አመታት ብዙ ጥረቶችን ስናደርግ ስናባብልም ቆይተናል ነገር ግን ይህ ሊያሳካው አልቻለም ሲሉም አንስተዋል፡፡

የባህር በርን የማግኘት መብት እና ሁኔታ በህጋዊ መንገድ መኖሩን መረዳት የሁሉም ኢትዮጲያዊ ድርሻ ነው ፤ ይህንን ሁሉም ዜጋ መቀበል እና ለዚህም ዝግጁ መሆን የግድ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ መውጫ መግቢያ በሯን ታበጃለች ይህ ጉዳይ የማይቀር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ይህ ሲሳካ ምናልባትም እኛ ላንኖር እንችላለን ነገር ግን ልጆቻችን በተዘጋ ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ድሃ ሳይሆኑ የታሪክ ሰሪ ልጆች ሆነው ከራሳቸው አልፈው ሌሎች ሀገራትን የሚያግዙ ይሆናሉ ነው ያሉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት “የመደመር መንግሥት” መጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ ሰላም አስቀድማ ድህነትን ትፋለማለች ብለዋል።

የውልሰው ገዝሙ

መስከረም 7/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *