የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የጋዛ ከተማ ነዋሪዎች ከስፍራዉ ለቀዉ እንዲወጡ ጊዜያዊ መንገድ ከፈተ

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ነዋሪዎች የተወሰነላቸዉን መንገድ ብቻ እንዲጠቀሙ እና በጸጥታ አስከባሪዎች የሚሰጡትን መመሪያዎች እንዲከተሉ ጠይቋል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ጊዜያዊ የመተላለፊያ ኮሪደር መክፈቱን ሲገልጽ፤ ይህም ሲቪሎች ከጋዛ ከተማ ወደ ዋዲ ጋዛ ደቡባዊ አካባቢዎች ለቀዉ እንዲወጡ ለማድረግ ነዉ ብሏል፡፡

ኮሪደሩ ከዛሬ መስከረም 07 ከቀኑ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ መስከረም 9 ከቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ነዋሪዎች የተወሰነውን መንገድ ብቻ እንዲጠቀሙ እና በጸጥታ አስከባሪዎች የሚሰጡትን መመሪያዎች እንዲከተሉ አሳስቧል።

ሰራዊቱ ሲቪሎችን ለመርዳት የትራፊክ ምልክቶች በመንገዱ ላይ እንደተቀመጡም አስታዉቋል፡፡

በጋዛ ከተማ ከሚኖሩት አንድ ሚሊየን ከሚገመቱ ነዋሪዎች ዉስጥ እስከ ማክሰኞ ድረስ በግምት 3መቶ50 ሺህ ነዋሪዎች ከጋዛ ከተማ ለቀው ወጥተዋል ሲል ሰራዊቱ ማስታወቁን የጀሩሳሌም ፖስት ዘገባ ያመላክታል፡፡

እስከዳር ግርማ

መስከረም 7/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *