በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 9መቶ46 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ተባለ፡፡

‎ትላንት እና ዛሬ በተደረገ 4 ዙር በረራ የተመለሱት 5መቶ69 ወንዶች፣ 3መቶ77 ሴቶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 45ቱ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸዉ፡፡

‎ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡

‎ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ፤ መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 1 ሺህ 46 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

መስከረም 8/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *