ጂሚ ኪመል በቻርሊ ኪርክ ግድያ ዙሪያ በሰጠዉ አስተያየት ከአየር ላይ መነሳቱ ተገለጸ

ኤቢሲ ቴሌቭዥን የምሽት ፕሮግራም አዘጋጁ ጂሚ ኪመልን ፤ ስለ ቀኝ ክንፍ ተፅዕኖ ፈጣሪው ቻርሊ ኪርክ ግድያ የሰጠውን አስተያየት ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ ከስርጭት አግዶታል።

የተሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የጂሚ ኪመል ፕሮግራም ከአየር ላይ ላልተወሰነ ጊዜ ይቋረጣል ይላል፡፡

ጂሚ ኪመል በዝግጅቱ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ኪርክን በመግደል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየተሞከረ ነው ብሏል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ‹‹ለአሜሪካ ታላቅ ዜና›› ነው ብለዋል።

ጂሚ ኪመል ፤ የማጋ ቡድን ቻርሊ ኪርክን የገደለውን ልጅ ከነሱ የተለየ ለማድረግ እና ከዚህ ግድያ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በከፍተኛ ሁኔታ እየሞከረ ነዉ ሲል አስተያየት ሰጥቷል፡፡

ለቻርሊ ኪርክ ክብር ለመግለጽ ባንዲራዎች ዝቅ ብለዉ እንዲዉለበለቡ መደረጉን ተችቷል፡፡የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለግድያው በሰጡት ምላሽም ተሳልቋል።

ኪርክ በተገደለበት ቀን ጂሚ ኪመል በኢንስታግራም ገጹ ላይ ጥቃቱን አዉግዞ፤ለ31 ዓመቱ አክቲቪስት ቤተሰብ “ፍቅር” መላኩን ገልጿል።

ኤቢሲ ኪመል ከስራ መታገዱን ካስታወቀ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ‹‹ኤቢሲ በመጨረሻ ማድረግ ያለበትን ለማድረግ ድፍረት በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ›› ሲሉ ጽፈዋል፡፡

አንድ የ22 ዓመት ወጣትም በቻርሊ ኪርክ ግድያ ወንጀል ተከሶ ፍርድ ቤት መቅረቡ ይታወቃል እንደ ቢቢሲ ዘገባ፡፡

እስከዳር ግርማ

መስከረም 08/2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *