ትግበራዊ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን እ.ኤ.አ በ2019 ከፈረሙ ሀገራት አንዷ ናት፡፡
ስምምነቱ የንግድ አጋሮችን ለማስፋትና በአፍሪካ አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
እ.ኤ.አ. 21 ማርች 2018 በኪጋሊ-ሩዋንዳ በ44 አገሮች የተፈረመው የአፍሪካ አህጉራዊ የነጻ ንግድ ቀጠና ስምምነት እስካሁን ድረስ ከ55 በላይ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን ከኤርትራ በስተቀር 54ቱ ሀገራት ፈርመውታል፡፡
በስምምነቱ የእቃዎች ንግድ ስምምነት ፕሮቶኮል አንቀጽ 7 እንደተደነገገው የገቢ ንግድ ቀረጥን አስመልክቶ ስምምነት በተደረሰበት የቀረጥ ሠንጠረዥ (Schedule of Tariff Concession) መሠረት ከስምምነቱ አባል ሀገራት የሚመነጩ ዕቃዎች ላይ የሚጥሏቸውን ቀረጦችና ተመሳሳይ ውጤት የሚያስከትሉ ሌሎች ክፍያዎች ደረጃ በደረጃ ማስወገድ እንዳለባቸው ይገልፃል፡፡
በተጨማሪም ከሌሎች የስምምነቱ አባል ሀገራት የሚመነጩ ዕቃዎች ላይ ማንኛውንም አይነት አዲስ የገቢ ንግድ ቀረጥ ወይም ተመሳሳይ ውጤት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎችን መጣል እንደማይችሉ ተደንግጓል።
እነዚህን እና ሌሎችንም የንግድ ስምምነቶች የሚካትተውን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ነው ኢትዮጲያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ የምታደርገው፡፡
መስከረም 19/2018 ዓ.ም
