ፍርድቤቱ በሬክ ማቻር ላይ የግድያ እና የሀገር ክህደት ክስን የመሰረተባቸው ሲሆን ሰውየው ይሄ ክስ ውድቅ እንዲደረግላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ሳይቀበል እንደቀረ ተናግረዋል፡፡
በደቡብ ሱዳን የሚገኘው ልዩ ፍርድ ቤት የታገዱት ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻርን እና በሰባት ተከሳሾች ላይ በነፍስ ግድያ፣ በሀገር ክህደት እና በሰው ልጆች ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ክስ የመመስረት ስልጣን እንዳለው ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡
ሪክ ማቻር ከሁለት ሳምንት በፊት የቀረበባቸውን ክስ ፖለቲካዊ ውሳኔ ነው ሲሉ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በፕሬዝዳንቱ ሳልቫኪር እና በምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩት ሬክ ማቻር መሃል የተፈጠረው አለመግባባት ደቡብ ሱዳንን ወደ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳያስገባት ከፍተኛ ስጋት እንደተፈጠረ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
መስከረም 20/2018 ዓ.ም
