የጀርመኑ መሪ ሜርዝ የትራምፕን የጋዛ ዕቅድ በደስታ መቀበላቸዉን ገለጹ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋዛ ሰላም እንዲሰፍን ያቀረቡት ሀሳብ በአከባቢው ያለውን ጦርነት ለማስቆም የተሻለ እድል ይሰጣል ሲሉ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ፍሬድሪክ ሜርዝ ተናግረዋል።

ጀርመን ለዕቅዱ ትግበራ ተጨባጭ አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ናት ያሉት የጀርመን መንግስት ቃል አቀባይ፤ ሜርዝ በትላንትናው ዕለት በሃማስ ከተያዙት የጀርመን ታጋች ቤተሰቦች ጋር ተገናኝተዋል።

ከጀርመኑ መሪ በተጨማሪ የአውሮፓ እና መካከለኛው ምሥራቅ መሪዎች አሜሪካ የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ያቀረበችውን የሰላም ዕቅድ እንደሚደግፉ አስታዉቀዋል።

የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ “ኔታንያሁ ለሰላም ዕቅዱ አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው አበረታች ነው” ብለዋል።

ሁሉም አካላት ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ለሰላም ዕድል መስጠት አለባቸው ሲሉም አክለዋል።

ለተኩስ አቁም ስምምነቱ ቅርብ የሆኑ የፍልስጤም ምንጭ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ዋይት ሀውስ ለሐማስ 20 ነጥቦችን አቅርቧል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐማስ ስምምነቱን መቀበል አለበት ብለዋል።

ትራምፕ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተስማሙበት ዕቅድ፤ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖች በአፋጣኝ እንዲቆሙ ያደርጋል ተብሏል።

ሐማስ በ72 ሰዓታት ውስጥ 20 እስራኤላውያን ታጋቾችን እና የሞቱ ታጋቾችን አስክሬን እንዲያስረክብ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።

በምላሹም በመቶዎች የሚቆጠሩ የታገቱ የጋዛ ነዋሪዎች ከእስር የሚለቀቁ ይሆናል ተብሏል።

ሀና ሰይፉ

መስከረም 20/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *