በምንጃር አረርቲ ማርያም ቤተክርስቲያን በደረሰው አደጋ እስካሁን የሰባት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ማጋጠሙ ተገልፃል፡፡
በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ማርያም የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ የ7 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ2 መቶ በላይ ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንዳጋጠማቸው የወረዳዉ ፖሊስ መምሪያ ለኢትዮ ኤፍኤም አስታዉቋል ፡፡
የወረዳዉ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኢንስፔክተር አህመድ ገበየሁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በቤተክርስቲያኑ የሚከበረውን አመታዊውን የቅድስት ድንግል ማርያም በአለ ንግስ አስመልክቶ እየተሰራ ያለው ቤተክርስቲያን እየተጎበኘ ባለበት ሰዓት ነው የተረበረበው እንጨት የመደርመስ አደጋ አጋጥሞት ከባድ አደጋ የደረሰው፡፡
ተጎጅዎችን አደጋ ከደረሰበት አካባቢ የማንሳት ስራ አሁንም እየተሰራ መሆኑን ያነሱ ሲሆን በመንግስት፣ በግል እና በመከላከያ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
መስከረም 21/2018 ዓ.ም
