የወታደር ልብስ የለበሱ የአልሸባብ ታጣቂዎች የሶማሊያ እስር ቤትን አጠቁ

ሰባት የአል ሻባብ ታጣቂዎች በሶማሊያ ዋና ከተማ የሚገኝ እና ጥብቅ ጥበቃ የሚደረግለት እስር ቤት ላይ ጥቃት ከሰነዘሩ በኋላ መገደላቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።

ቅዳሜ ማታ የአልሸባብ ታጣቂዎች ታስረውበት በሚገኘው ጎድካ ጂሊኮው ተብሎ የሚጠራው ማረሚያ ቤት ከሚገኝበት አካባቢ ከፍተኛ የፍንዳታ እና የተኩስ ድምጽ ተሰምቶ ነበር።

አል ሻባብ ባወጣው መግለጫ በማረሚያ ቤቱ ታስረው የነበሩ “ሁሉንም ሙስሊም እስረኞች” ማስለቀቀቁን እና ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።

በመንግሥት የሚተዳደረው ሶና የዜና ወኪል በበኩሉ እሁድ ዕለት እንደዘገበው፤ ታጣቂዎቹ ወደ ማረሚያ ቤቱ ለመግባት የአገሪቱን ወታደር የደንብ ልብስ ለብሰው እንደነበር ገልጿል።

መንግሥት ምን ያህል የፀጥታ አባላት እንደተገደሉበት ያልገለፀ ቢሆንም “ለተሰዉ ጀግኖች” ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል።

መስከረም 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *