የአደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ምላሽ አሰጣጥ መረጃዎች የተቋማትን መናበብ የሚጠይቁ እንዲሆኑ ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኢትዮጵያ የሚከሰቱ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃ እንዴት ይተላለፍ ? በሚል የዉይይት መድረክ አካሂዷል።

በዚህ ዉይይት ላይ የፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን ፣የመገናኛ ብዙሃን ፣የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋማት እና የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የአደጋ ስጋት ኮምሽኑ እና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማቱ በተለይም ለቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች በማሰራጨት ረገድ በተናበበ መንገድ መስራት ላይ ክፍተቶች እንዳሉባቸዉ በዉይይቱ ላይ ተነስቷል።

የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ለማሰራጨት የተቋማቱ አለመተማመን÷ የመረጃዉ ግልፀኝነትና እንዲሁም የአደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን ባለሙያዎች ተጠያቂነት የመረጃዉ ተደራሽነት ላይ እክል መሆኑም በዉይይቱ የቀረበ ሀሳብ ነዉ።

የአደጋ ስጋት ኮምሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሀኑ የሚሰጡበት አግባብ እንዲሁም የመገናኛ ብዙሃኑ የሚያስተላፉበት መንገድ ቀድሞ መናበብ የሚያስፈልገዉ እንዲሆን ተጠይቋል።

ዉይይቱን ያሰናዳዉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአደጋ ስጋት አመራር መምሪያ ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ አቶ ጋሻዉ ዳኜ፤ መገናኛ ብዙሃኑና የቴሌኮም ተቋማት ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ተዋንያን ጋር በቅንጅት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

የዜጎችን ህይወት እና ንብረት ቀድሞ ለመታደግ እና አደጋዉን በተወሰነ ለመቀነስ እንዲያስችል የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ትኩረት እንዲያገኙ እንደሚያስፈልግ በመድረኩ ተነስቷል።

የአለም አቀፍ ልምዶችን በመጠቀም እና ሌሎች የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ተደራሽነት ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲኖሩ ተመክሯል።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *