የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሴባስቲን ሌኮርኑ ካቢኔያቸው ይፋ ከሆነ አንድ ቀን እንኳን ሳይሞላው ስልጣን ለቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ እንድቀጥል ቅድመ ሁኔታዎች አልተሟሉልኝም ያሉት ሌኮርኑ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት ላይ ለመድረስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተችተዋል።

ሌኮርኑ ሰኞ ማለዳ ላይ ለአንድ ሰአት ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ከተገናኙ በኋላ ይህ ዉሳኔ ይፋ መደረጉ ተገልጿል።

ይህ ዉሳኔ የመጣው ሌኮርኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ ከተሾሙ ከ26 ቀናት በኋላ ነው።

በብሔራዊ ምክር ቤት ውስጥ ያሉ የቦርዱ ፓርቲዎች የሌኮርኑ ካቢኔ ውቅር ከድሮው ብዙም ያልተቀየረ መሆኑን በመግለፅ ውድቅ እንደሚያደርጉት ዝተዋል።

በሀገሪቷ የሚገኙ ብዙ ፓርቲዎች ቀደም ብለው ምርጫ እንዲደረግ እየጠየቁ ነዉ፡፡

ምንም እንኳን ማክሮን የስልጣን ዘመናቸው በ2027 ከማብቃቱ በፊት እንደማይነሱ ደጋግመዉ ቢናገሩም፤ አንዳንዶቹ ማክሮን ስልጣን እንዲለቁ እየጠየቁ ነዉ፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ማክሮን አገሪቱን እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አስገብተዋታል በማለት በተደጋጋሚ ሲነገሩ ይደመጣል፡፡

ሀና ሰይፉ

መስከረም 26/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *