የሱዳን ሚሊሻ መሪ ከዳርፉር ጦርነት ጋር በተያያዘ በጦር ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

የሱዳን ሚሊሻ መሪ ከ20 ዓመታት በፊት በዳርፉር ግዛት የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው ጥፋተኛ ተባሉ።

አሊ ሙሐመድ አሊ አብድ-አል-ራህማን ወይም አሊ ኩሻይብ በመባል የሚታወቁት ግለሰብ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከገደለው የጃንጃዊድ መሪዎች አንዱ ነበሩ።

ጃንጃዊድ በመንግሥት የሚደገፍ ቡድን ሲሆን ዳርፉርን በማሸበር ይታወቃል።

ኩሻይብ፤ በዳርፉር ከተፈፀመው ወንጀል ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ የቀረበባቸው የመጀመሪያው ግለሰብ ናቸው የተባሉት ግለሰብ “እኔ አይደለሁም” ሲሉ ተከራክረዋል።

እ.አ.አ ከ2003 እስከ 2020 ድረስ በዘለቀ ግጭት በዓለም ላይ ከተፈጠሩት ከባድ የሰብአዊ አደጋዎች አንዱ ነው።

በአካባቢው አረብ ባልሆኑ ሕዝቦች ላይ የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል።

የቀደመው ቀውስ ካበቃ ከአምስት ዓመታት በኋላም ዳርፉር በሌላ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ቁልፍ የጦር ሜዳ ሆናለች።

በአሁኑ ወቅት በሱዳን ጦር እና መነሻውን ከጃንጃዊድ ሚሊሻ ባደረገው በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) መካከል ጦርነት እየተካሄደ ነው እንደ ቢቢሲ ዘገባ።

መስከረም 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *