እንደሀገር የተፈጥሮ ጋዝ ማምረት መጀመሩን ተከትሎ የትራንስፖርት ዘርፉን በተፈጥሮ ጋዝ ወደሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለማሸጋገር አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል ያለው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ነዉ።
በቀጣይም በተፈጥሮ ጋዝ የሚንቀሳቀሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እና እንዲሰሩ መፈቀዱን አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በተፈጥሮ ጋዝ የማይሰሩ ከባድ መኪናዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይፈቀድ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በአክብሮት እናሳውቃለን ብሏል።
በመሆኑም አስመጪዎች ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የማስገባት ፍቃድ ሳታገኙ ምንም አይነት ከባድ መኪና ግዢ እንዳትፈጽሙ ተከልክሏል፡፡
በተጨማሪም ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በኋላ የሚደረጉ ግዥዎች የማስገቢያ ፈቃድ የማይሰጣቸው በመሆኑ በተፈጥሮ ጋዝ በሚንቀሳቀሱ ከባድ መኪናዎች ብቻ የተገደቡ እንዲሆኑም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
