አዲስ ይፋ የሆነው ሲሰትም ሁሉንም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችንም ግልጽ የሚያደርግ፣ዘርፉን ወደኃላ ሲያስቀሩ የነበሩ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ የሚያስችል ሲስተም መሆኑንም ሰምተናል።
“ኮንስትራክሽን ሪጉላተሪ ኢንፎርሜሽን ሲስተም” የተባለዉ ይህ ፕሮግረም፤ በኢትዮጽያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አማካኝነት የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጿል።
የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከ20 በመቶ በላይ ለሀገሪቱ ጂዲፒ አስትዋጽኦ እንዳለዉ የተናገሩት በመድረኩ የተገኙት የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፤ ዘርፉ ከዚህ ባለፈም ለመቶ ሺዎች የስራ እድል ፈጥሯል ብለዋል።
ሚኒስትሯ ከዚህ በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪዉን ዲጂታል ማድረግ በዘርፉ ያሉ ችግሮቹን ለመቅረፍ ሁነኛ መፍትሔ ሆኖ መቀጠሉንም አንስተዋል።
የኮንስትራክሽን እቃዎችን በሀገር ዉስጥ ለመተካትም በተለይም ደግሞ የፊኒሺንግ እቃዎችን በተመለከተም የሚታየዉን ችግርም እንደሚቀርፍም ተገልጿል።
አዲስ ይፋ የሆነው ፕሮግራም ግልጽነትን በደንብ ለማስፈንም እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በቴክኖሎጂ መደገፍ የሚጠበቅበት እንደሚሆንም ተሰምቷል።
ለአለም አሰፋ
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
