የሸገር ደርቢ 19ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ህዳሴ ዋንጫ በግማሽ ፍፃሜ ኢትዮጲያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 9:30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተጠባቂ ጨዋታቸውን ይደርጋሉ ።
ከአምስት አመታት ቆይታ በኋላ ዘንድሮ እግር ኳሱ ዳግም ወደ መዲናዋ ሲመለስ ሁለቱ ቡድኖች ለህዳሴ ዋንጫ ለፍፃሜ ለመብቃት በበርካታ ደጋፊዎቻቸዉ ታጅበዉ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያው ሳምንት ኢትዮጲያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዳግም የሚገናኙ በመሆኑ የዛሬዉን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል።
በሌላኛዉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል ቀን 7 :00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የስታዲየም መግቢያ ትኬቶቹ በቴሌብር አማካኝነት እየተሸጡ ይገኛሉ።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 29/2018 ዓ.ም
