በ2030 500 ሺህ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች በኤሌትሪክ የሚሰሩ ለማድረግ እቅድ ተይዟል ተባለ

ይህ የተገለጸዉ “የአፍሪካ ኢ_ሞብሊቲ ሳምንት”በይፋ ዛሬ በተከፈተበት ወቅት ነዉ

በሀገሪቱ ያለውን የታዳሽ ኃይል አቅም በአግባቡ ለመጠቀም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ዕቅድ መያዙን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታዉ ይህንን ያለዉ የአፍሪካ ኢ- ሞቢሊቲ ሳምንት በተካሄደበት ወቅት ነዉ።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን እንደገለፁት የሀገሪቱን የታዳሽ ኃይል አቅም መጠቀም የሚችል የትራንስፖርት ዘርፉ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ ነው፡፡

በተለይ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ለመጨመር ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

እንደ አቶ በርኦ ገለጻ፤ በነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን መጠቀም በዓመት እስከ 6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚስወጣ ተነስቷል ።

ከለውጡ ወዲህ መንግሥት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ ባደረገው የቀረጥ ማበረታቻና በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር እየገቡ ነው።

በዚህም በአፍሪካ አካታች እና ዘላቂ ትራንስፖርት ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በፖሊሲ፣ በፋይናንስ እና በአህጉሪቱ ዜሮ ልቀት ትራንስፖርት ትግበራ ዙሪያ ያተኩራል የተባለው መድረክ በይፋ ተከፍቷል።

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *