የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን አዕምሯዊ ንብረትን የሚመለከቱ መብቶችን ምዝገባ እያካሄደ እንደሆነ ገለፀ።

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ብሩክ ወርቅነህ፤ ቀደም ብለዉ የነበሩ መብቶችን ዘመኑ ለደረሰበት የአዕምሯዊ ንብረት ሁኔታ ምቹ ለማድረግ አዋጆችን በማሻሻል ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አዋጆቹን ማሻሻል የተፈለገዉ ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ጥረት እያደረገች መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ አንስተዋል።

የማቋቋሚያ አዋጁንና የአነስተኛ ፈጠራ አዋጅ ንድፍ በባለሙያዎች ተፈትሾና ረቂቁ ተዘጋጅቶ ለመንግስት እንዲቀርብ መደረጉንም አቶ ብሩክ ነግረውናል።

በተጨማሪም የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣናን ሀገራችን መቀላቀሏን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አፍሪካ ሀገራት የተወሰኑ ምርቶችን እየላከ መሆኑን ገልጸዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *