የአዲስ አበባ ከተማ ዕለታዊ የዉሃ አቅርቦት መጠኑ ላይ 62ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ጭማሪ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የዉሀ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በዚህ ዓመት ተጨማሪ አዳዲስ የዉሀ ፕሮጀክቶች ሊጨመሩ መሆኑም ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አምስተኛ አመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምክር ቤቱ ላነሳዉ የዉሃና የመብራት ጥያቄ፤የዉሀ አጠቃቀም ብክነት ጫና መሆኑን አንስተዉ በተያዘዉ በጀት አመት ተጨማሪ የዉሀ ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነዉ በሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ዕለታዊ የዉሀ አቅርቦት ላይ በአሁኑ ወቅት ወደ 62 ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ጭማሪ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

የዉሀ አቅርቦትን ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የቁጥጥር ስራዎች አለመኖራቸዉን እንደተግዳሮት ያነሱት ከንቲባዋ፤ የመጠጥ ዉሀ ለግንባታ፣ለመኪና ማጠቢያ እንዲሁም ለተለያዩ ነገሮች ጥቅም ላይ ይዉላል ብለዋል፡፡

ይህንን ለማስቀረትም ከተማ አስተዳደሩ የፍሳሽ ማጣሪያ ማዕከላትን በመገንባቱ ለዚህ አገልግሎትከዛዉ መጠቀም እንዳለባቸዉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፍብሪካዎችና ትልልቅ ተቋማትም የመጠጥ ዉሃን ከመጠቀም ይልቅ፤የዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፍቃድ ስለሚሰጥ የጉድጓድ ዉሀ መቆፈር እንዳለባቸዉ አሳስበዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *