የ92 ዓመቱ ፖል ቢያ የካሜሩንን ሀገራዊ ምርጫ አሸንፈዋል ሲል የሀገሪቱ ምርጫ ኮሜቴ ገልጿል።
ፕሬዝዳንት ቢያ ምርጫውን አሸነፉ የተባሉት 53.6 በመቶ ድምጽ በማግኘት እንደሆነ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ ዋና ተቀናቃኛቸው ኢሳ ባካሪ ማግኘት የቻሉት 35 በመቶ ድምጽ ነው ሲል የካሜሩን ምርጫ ኮሜቴ አሳውቋል፡፡
ይህ ምርጫ ፖል ቢያን ለስምንተኛ የሥልጣን ዘመን እድል የሰጠ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ሕገ-መንግሥታዊ ምክር ቤቱ በመጪዎቹ ቀናት የመጨረሻውን ውጤት በይፋ ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የፕሬዝዳንቱ ፖል ቢያ ሴት ልጅ ብሬንዳ ቢያ አባቷ በምርጫው መወዳደራቸውን በመቃወም ካሜሩናውያን ለ92 ዓመቱ አዛውንት ድምፅ እንዳሰጡ በይፋ መጠየቋ ይታወሳል፡፡
የፕሬዝዳንቱ ልጅ በአባቷ የ43 ዓመታት የስልጣን ዘመን በካሜሩን ድህነትና ስራ አጥነት መስፋፋቱን በመግለፅ ነበር ካሜሩናውያን ለፖለ ቢያ ድምፃቸውን እንዳይሰጡ የጠየቀችው፡፡
ይህም በአፍሪካ የፖለቲካ ታሪክ በስልጣን ላይ የሚገኝ ፕሬዝዳንት ልጅ በይፋ ለቤተሰቧ አውራ ድምፅ እንዳትሰጡ የሚል ተቃውሞ በማሰማት የመጀመሪያዋ አድርጓታል፡፡
አዲስአለም አበበ
ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም
