በክልሉ በነበሩ ችግሮች የመማር ማስተማር ሂደታቸው የተስተጓጐሉ ትምህርት ቤቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ዘግይቶም ቢሆን ተማሪዎችን የመመዝገብ ሂደት እየተከናወነ መሆኑን የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል ።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ስዩም ሀጎስ በምዕራብ ትግራይ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ 75 ትምህርት ቤቶች ግን ወደ ስራ መመለስ አለመቻላቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
አዲሱን የስርዓተ ትምህርት በሚቀጥለው ዓመት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል።
እንዲሁም ከ9ኛ – 12ኛ ክፍል ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጥንድ ጥንድ በማድረግ ከፌደራል መንግስት በተገኘ የመፃህፍት አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ ቢቻልም ፤የአንደኛ ደረጃ ላይ ያለው የመፅሀፍ አቅርቦት ግን አናሳ ነው ብለዋል።
በክልሉ ያለውን የትምህርት ሁኔታ ለማሻሻል እና ዜጎችን ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን እንዲወጣ አቶ ስዩም ጥሪ አቅርበዋል።
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
