የካሜሩን ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ዛሬ በሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት የምርጫ አሸናፊ ሆነው የተገለጹ ሲሆን፤ 53.66 በመቶ ድምፅ በማግኘት አሸንፈዋል ተብሏል።
የ92 ዓመቱ አዛዉንት ለ43 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን፤ ስምንተኛ የስልጣን ዘመን ያገኙት ዋና ተፎካካሪያቸውን የቀድሞውን ሚኒስትር ኢሳ ቲቺሮማ ባካሪን በማሸነፍ ነው።
ቲቺሮማ 39.19 በመቶ ድምፅ በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ይሁን እንጂ ቲቺሮማ በጥቅምት 12 በተካሄደው ምርጫ ማሸነፋቸውን ሲናገሩ ቆይተዋል።
ደጋፊዎቻቸው እሁድ ዕለት በዱዋላ ትልቁ ከተማ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን፤ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ አራት ሲቪሎች ሕይወታቸውን አጥተዋል መባሉን አናዶሉ አስነብቧል።
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
