የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከአላስካው የሰላም ስምምነት እያፈገፈጉ ነው ስትል ሩስያ ከሰሰች።

የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርገይ ላብሮቫ ይህን ክስ ያቀረቡት ፕሬዝዳን ትራምፕ በሩስያና ዩክሬይን መካከል የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ ይቁም ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለአንድ የሐንጋሪ መገናኛ ብዙኀን የሰጡትን ቃለ ምልልስን ጠቅሶ የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው የአላስካው ስምምነት ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት ማድረግን ዓላማ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ትራምፕ ግን በተጻራሪው አሁን አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ መፈለጋቸውን ወቅሰዋል።

ላቭሮቭ አክለውም የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የአላስካው ስምምነትን በተመለከተ የአሜሪካን አቋም የተቀበሉት ለድርድርና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ያስችላል በሚል መንፈስ መሆኑንና ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዳልሆነም ነው የገለጹት።

የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ከአላስካው ስምምነት በኋላ ሩስያ በዩክሬይን የፈጸመቻቸውን ጥቃቶች እንደሚያሳስባቸው በመግለፅ በሩስያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣላቸው ይታወሳል።

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *