የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ኬንያን ሊጎበኙ ነው።

ጄዲ ቫንስ በመጪው ታኅሣሥ ወር በደቡብ አፍሪካ በሚካሄድ አንድ ጉባኤ ላይ ከተካፈሉ በኋላ ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ የውስጥ ምንጮችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በኬንያ ስለሚያደርጉት ጉብኝትም ሆነ ስለሚኖራቸው ቆይታ በዝርዝር የተባለ ነገር የለም።

ከአሜሪካ ጋር የቅርብ ትብብር እንዳላት የሚነገርላት ኬንያ የተያዘው ዓመት ከመጠናቀቁ በፊት የንግድ ስምምነት የመፈጸም ዕቅድ እንዳላት ተነግሯል።

አሜሪካ ባለፈው ዓመት የ2024 ኬንያን የኔቶ አባል ሀገር ያልሆነች ሁነኛ አጋር በማለት መሰየሟ ይታወሳል።

እንደዚያም ሆኖ ግን ኬንያ በተለይ ከቻይና ጋር ያላት የጠበቀ ግንኙነት በአሜሪካ ባለስልጣናት ዘንድ የተወደደላት አይመስልም። የተለያዩ ባለሥልጣናት በተለያዩ ጊዜያት በዚሁ ጉዳይ ላይ ትችት ሲያቀርቡባት ቆይተዋል።

ይሆን እንጂ ምክትል ፕሬዚዳንት ጂዴ ቫንስ ከታኅሣሥ 3 እስከ 7 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ በናይሮቢ የጉብኝት ቆይታ እንደሚኖራቸው ምንጮች ነግረውኛል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል።

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *