ከምክር ቤቱ አባላት ከተነሱ ጥያቄዎቸ እና አስተያየቶች መካከል፤
በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ያሉ ታጣቂዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ማህበረሰቡ በሰለም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ መንግስት እየሰራቸው ያሉ ስራዎች ምን እንደሆኑ ማብራሪያ ቢሰጥ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትስ መንግስትስ ምን ያህል ቁርጠኛ ነው?
የትግራይ ክልል ሁኔታ ምን መሆን አለበት?በትግራይ ያሉ አንዳንድ አካላት የክልሉን ብሎም የሃገሪቱን ሰላም ለማወክ እየሰሩ ያሉ አንጃዎችን አደብ ማስያዝ ለምን አልተቻለም?
የኢትዮጵያን ሰላም ለመበጥበጥ ከውጭ አካላት በተለይም ከኤርትራ ጋር የሚሰሩ በተለይ በትግራይ ያሉ ሃይሎችን ሴራቸውን ለማክሸፍ ምን አይነት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ?
የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር መንግስት ተደጋጋሚ ስራዎችን ቢሰራም በቅርቡ የተደረገውን የደሞዝ ጭማሪ አስመለክቶ ስግብግብ ነጋዴዎች እንዲሁም የቤት አከራይ ማህበረሰቦች አላግባብ ጭማሪ እያደረጉ ስለሆነ እነሱን ለመቆጣጠጠር ምን እየተሰራ ነው?
የባህር በር ጥያቄን ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር እንዴት ይታያል፤ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡም ይህ ጉዳይ ሰላማዊ እና ህልውና ጥያቄ እንደሆነ እንዲገነዘቡ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቢገለጹ፤
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትለው የመጡ አንዳንድ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ምን እየሰራ ይገኛል?
የቤት ችግርን ለመፍታት እና የቤት አቅርቦትን ለመጨመር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ መንግስት ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ለምክር ቤቱ ቢነሱ?
ሰባተኛውን ሃገራዊ ምርጫ በተመለከተ የሀገራዊ ምክክሩ ውይይትም በዚሁ አመት እንደሚደረግ ስለሚታወቅ በሀገራዊ ምክክሩ ሲነሱ የነበሩ ሃሳቦች ሳይመለሱ ወደ ምርጫ መሄዱ በታዓማኒነቱ ላይ ጥያቄ አያስነሳም ወይ ይሄ በምን መልኩ ታስቧል?
የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ምን እየተሰሩ ነው? እንዲሁም መምህራንን አቅም ለማሻሻል እንዲሁም የመምህራንን ችግሮች ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው?
ከምክር ቤቱ አባላት እየቀረቡ ባሉ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
ለዓለም አሰፋ
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
