“ኢትዮጵያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ ትገኛለች የተባለው አውነት ነው ግን በቁጥር ማየት ጠቃሚ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዶ/ር

ይህ የተገለጸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ነው

ኢትዮጵያ በከፍተኛ እዳ ውስጥ ትገኛለች የተባለው አውነት ነው ግን በቁጥር እና በንጽጽር ማየት ጠቃሚ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አፍሪካ ውስጥ አንድኛ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት ከፍተኛ ብድር አለባቸው በንጽጽር ሲታይ ግን ቁጥሩ የኛ የተሸለ ነው ብለዋል፡፡

የእኛ ብድር አስቸጋሪ የሆነው ብድሩን የወሰድንበት መንገድ ነው የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስተሩ፤ የወሰደንው ብድር ኮሜርሻል ሎን ስለሆነ ለመክፈል አስቸጋሪ በመሆኑ እንጂ ብድሩ ብዙ ሆኖ አይደልም ሲሉ አክለዋል፡፡

አበዳሪ አካላት እድገታችንን እያዩ ስለሆነ እንዳለ ያለብንን ብድር እንደንከፍል ይፈልግሉ እኛ ግን በመርሁ መሰረት ነው ምንከፍለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የለውጡ መንግስት በዚህም አንድም ዶላር በኮሜርሻል ሎን ሳይውስድ ነው እስካሁን ያለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ስኬት ነው ብለዋል

በዚህ አመት 1ትሪሊየን ብር ገቢ እንደሚጠበቅ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህም የማክሮ አኮኖሚ ማሻሻያ ጥቅም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *