አውሎ ነፋሱ ወደ ሰሜን ምስራቅ በመጠምዘዝ ወደ ኩባ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ ሳንቲያጎ ዴ ኩባ እንዳመራ ተገልጿል፡፡
በኃይለኝነቱ በምድብ አራት የተቀመጠዉ ይህ አዉሎንፋስ፤ጎረቤት ጃማይካን በመምታት እስካሁን በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ሆኖ ተመዝግቧል።
በደቡብ ምዕራብ ጃማይካ፣ ከ5መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች ያለ ኤሌክትሪክ ቀርተዋል ሲሉ የአከባቢዉ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የጃማይካ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሪው ሆልነስ፤ እስካሁን ያገኘናቸው ሪፖርቶች የሚያሳዩት፤ በሆስፒታሎች፣በመኖሪያ አከባቢዎች ፣በመኖሪያ ህንጻዎች፣ በንግድ ቤቶች እና ንብረቶች እንዲሁም በመንገድ መሠረተ ልማቶቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዉ ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ከአዉሎ ንፋሱ ጋር በተገናኘ ሞት እንዳልደረሰ ገልጸዉ፤ ነገር ግን የአውሎ ነፋሱን ጥንካሬ እና የጉዳቱን መጠን ከግምት ውስጥ በማስገባት ‹‹የህይወት መጥፋት እንደሚኖር እንጠብቃለን›› ሲሉ መናገራቸዉን ሲኤን ኤን ነዉ የዘገበዉ፡፡
እስከዳር ግርማ
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
