በሰሜን አፍጋኒስታን 6.3 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ የሰባት ሰዎችን ህይወት መንጠቁ ተገለጸ

ዛሬ ማለዳ ላይ በሰሜናዊ አፍጋኒስታን ማዛር-ኢ ሻሪፍ አቅራቢያ የተከሰተዉ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሰባት ሰዎችን ገድሎ 1መቶ50 የሚያህሉ ሰዎችን አቁስሏል ሲሉ የክልል ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡

የሟቾች ቁጥር ዛሬ ማለዳ በተሰበሰበ የሆስፒታል ሪፖርት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ እና አደጋው በሰፊው ሊሰራጭ ይችላል ሲል አመልክቷል።

የሀገሪቱ ብሄራዊ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ የሟቾችን ቁጥር እና በደረሱ ጉዳቶች ላይ ሪፖርቶችን እንደሚያጋራ አስታዉቋል ሲል የዘገበዉ ሮይተርስ ነዉ፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *