በሩሲያዋ ካንቲ-ማንሲስክ ከተማ የሚገኝ አንድ የፋብሪካ ሰራተኛ፤በሶፍትዌር ችግር ምክንያት በስህተት የተላከለትን ከ7 ሚሊየን ሩብል ወይም 87 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በኩባንያው ክስ ቀርቦበታል።
ይህ ቭላድሚር ሪቻጎቭ የተባለው ግለሰብ ከባንኩ ማሳወቂያ መልዕክት ሲደርሰው ዓይኖቹን ማመን አልቻለም።
እሱ ወደ ባንክ አካውንቱ እንደሚገባለት ከሚያውቀው 46 ,954 ሩብል /581 ዶላር በተጨማሪ፣ 7,112,254 ሩብል /87,000 / ዶላር የሆነ ከፍተኛ ብር ሊገባለት ችሏል።
ፋብሪካቸው በስራ ስኬታማ ዓመት በማሳለፉ ከፍተኛ የሆነ ጉርሻ እያዘጋጀላቸው እንደሆነ በሥራ ባልደረቦቹ መካከል ወሬዎች ቢኖርም ግን እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አልጠበቀም።
ይሁን እንጂ ሚሊየነር የመሆን ደስታው ብዙም አልቆየም፤ ምክንያቱም ከፋብሪካው የሂሳብ ክፍል በስህተት 7 ሚሊዮን ሩብል እንደተላለፈለት እና መመለስ እንዳለበት ተነገረው።
ሪቻጎቭ ግን አንዳንድ ምርምር በማድረግ ሳይስማማ ቀርቷል፡፡
ግለሰቡ ተጠይቆ በሰጠው ምለሽም፤ ቴክኒካዊ ስህተት ከሆነ የመመለስ ግዴታ የለብኝም ነበር፣ የክፍያ ስህተት ከሆነ ግን የመመለስ ግዴታ ነበረብኝ ሲል ተናግሯል።
በኋላ ላይ ቴክኒካዊ ስህተት እንደሆነ ተረዳሁና ገንዘቡን የማስቀመጥ መብት እንዳለኝ ወሰንኩ ብሏል፡፡
በአሰሪው የቀረቡ የፍርድ ቤት ሰነዶች እንደሚያሳዩት፤ ገንዘቡ የ34 ሰራተኞችን ደሞዝ ለመክፈል የታሰበ ነበር ሆኖም በሶፍትዌር ችግር ምክንያት በስህተት ወደ ሪቻጎቭ ተላልፏል ስለዚህ እሱ የመመለስ ግዴታ ነበረበት የሚል ነው፡፡
የፋብሪካ ሀላፊው ጉርሻ የሚባል ነገር አልነበረም፤ የተሳሳተ ዝውውር ነበር ፡፡
የፍርድ ቤት ትዕዛዝም አለን፤ የእሱ አተረጓጎም እንግዳ ቢሆንም፣ ነገሩን የህግ ስርአቱን ተከትለን እንፈታዋለን ስለማለታቸው ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም
