በኔፓል በደረሰ የበረዶ ናዳ አደጋ የሰባት ተራራ ወጪዎች ህይወት አለፈ

የነፍስ አድን ሰራተኞች ሌሎች የውጭ ሀገር ዜጎችን እና የሀገር ውስጥ አስጎብኚዎችን ያካተተውን ቀሪ ቡድን የማፈላለግና የማዳን ስራ እየሰሩ ይገኛል።

በሰሜን ምስራቅ ኔፓል ሂማሊያ ከፍታ ላይ በደረሰ የበረዶ መንሸራተት አደጋ አምስት የውጭ ሀገር ዜጎች እና ሁለት ኔፓላውያንን ጨምሮ ቢያንስ ሰባት ተራራ ወጪዎች ህይወታቸው አልፏል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች ሁለት አስከሬኖችን ያገኙ ሲሆን፤ በበረዶ እንደተቀበሩ የሚታመኑትን የተቀሩትን አምስት ሰዎች በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ።

እስካሁን ሌሎች ስምንት ሰዎች ከሞት ተርፈው በዋና ከተማዋ ካትማንዱ ህክምና እያገኙ ነዉ ተብሏል፡፡

የሌሎቹ አምስት የሟቾች አስከሬን ከበረዶው ከ10 እስከ 15 ጫማ በታች ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን፤ እነሱን ለማግኘት ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ነዉ የተገለጸዉ፡፡

በበረዶ ናዳው ህይወታቸውን ያጡት 2 የጣሊያን፣ 1 የካናዳ፣ 1 የጀርመን እና ፣ 1 የፈረንሣይ ዜግነት ያላቸዉ ጎብኚዎች እና 2 በአስጎብኚነት ሲያገለግሉ የነበሩ ኔፓላውያን ናቸዉ ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡

ሀና ሰይፉ

ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *