የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም አበራ፤ በምርቶቹ ላይ ያሉት ዝርዝር መረጃዎች ግልጽ ባለመሆናቸዉ ማህበረሰቡ በቀላሉ ተረድቷቸዉ እንዳይጠቀም አድርጓል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በታሸጉ ምግቦች ሽፋን ላይ በውስጣቸው የያዙት ንጥረ ነገር በዓይነት እና በመጠን በግልጽ ሊቀመጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሰዎች የታሸጉ ምግቦችን ሲመገቡ ሊደርስባቸው የሚችሉ ጉዳቶች በመሸፈኛቸው ላይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ሊረዳቸዉ በሚችለዉ ቋንቋና ቀለም መቀመጥ አለባቸው ሲሉ አቶ ቢኒያም አስረድተዋል።
አክለዉም በታሸጉ ምግቦች ላይ በቂ ቁጥጥርና ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑ የታሸጉ ምግቦችን መቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ የተገለጸ ሲሆን፤የዚህ አዋጅ መፅደቅ ማህበረሰቡን ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች በመከላከል ረገድ ጉልህ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።
ልዑል ወልዴ
ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም
