በእድሳቱ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ የተሻሻሉ የመብራት እና የደኅንነት ሥርዓቶች መሰናዳታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
አፄ ፋሲል፣ የአፄ ቀዳማዊ ዮሃንስ እና አፄ ቀዳማዊ ኢያሱ አቢያተ መንግሥት፣ድልድዮች፣ መታጠቢያ ሥፍራዎች፣
ታሪካዊ በሮች እና ሌሎችም እንደታደሱ አመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም ከ40,000 ስኴር ሜትር በላይ በአካባቢው ምድር የማስዋብ ሥራ መሠራቱን እና ይኸም ለጎብኝዎች ይበልጥ ሳቢ የሆነ ከባቢ እንደፈጠረ አክለዋል፡፡
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም
