ፈረንሳይ ለዩክሬን የጦር አውሮፕላኖችን ልትሸጥ ነው

የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮን እና የዩክሬኑ አቻቸዉ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በፓሪስ ታሪካዊ የተባለውን የመከላከያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የፈረንሳይን እጅግ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች የሆኑትን እስከ 100 የሚደርሱ ራፋሌ ተዋጊ ጄቶች ለዩክሬን ለመሸጥ የሚያስችል የ10 ዓመት ስትራቴጂያዊ የትብብር ሰነድ ይዟል።

ዩክሬን እስከ 100 የሚደርሱ ፈረንሳይ ሠራሽ ራፋሌ ኤፍ 4 ተዋጊ አውሮፕላኖች እንዲሁም የተሻሻሉ የአየር መከላከያዎችን ታገኛለች፡፡

እነዚህ የጦር መሣሪያዎች ኪየቭ ራሷን ከሩሲያ ከባድ ጥቃቶች የመከላከል አቅሟን ለማሳደግ ያስችሏታል ተብሏል።

የጄቶቹ አቅርቦት እስከ 2035 ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፤ የዩክሬንን የድህረ-ጦርነት አየር ኃይል የመገንባት ግብ አለው።

የጠላትን አውሮፕላኖች እንቅስቃሴ የሚጠልፉ ድሮኖችን በጋራ ማምረት በዚህ ዓመት ይጀመራል ተብሏል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ አቅራቢያ በሚገኝ የአየር ማረፊያ ስምምነቱን የያዘ ሰነድ ከተፈራረሙ በኋላ እርምጃውን ‹‹ታሪካዊ›› ሲሉ አድንቀዋል።

እስካሁን ድረስ የጦር መሣሪያዎችን ግዢ ወጪ ለመሸፈን የገንዘብ ምንጭ ከየት እንደሚገኝ ያልታወቀ ቢሆንም፤ፈረንሣይ የአውሮፓ ኅብረት ድጋፍን ለማግኘት እና የታገዱ የሩሲያ ንብረቶችን ለመጠቀም አቅዳለች።

ይህ ስምምነት ዩክሬን ከጊዜ ወደ ጊዜ ከሶቪየት ኅብረት ዘመን የጦር መሣሪያዎች ተላቃ ሙሉ በሙሉ ወደ ምዕራባዊ የጦር መሣሪያ ስርዓት እንድትሸጋገር ይረዳታል።

ዩክሬን በጠቅላላ 2መቶ50 ዘመናዊ ተዋጊ ጄቶች ለማግኘት ዕቅድ ያላት ሲሆን፤ ከፈረንሳይ ራፋሌ ጄቶች በተጨማሪ ከስዊድን ግሪፐን እና ከአሜሪካ ኤፍ-16 ጄቶችን ለማግኘት በትይዩ እየሰራች ነው ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል።

ሱፊያን አህመድ

ህዳር 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *