የዓለም የጥራት ሳምንት በኢትዮጵያ ከመጪው ህዳር 11-14 ይከበራል

በዘንድሮው ዓመት “ጥራት በተለየ እሳቤና ፈጠራ” በሚል መሪ ቃል የጥራት ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዕለቱን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ከ1መቶ50 እስከ 2መቶ የጥራት ማረጋገጫ ያገኙ ድርጅቶች ከ1መቶ20 ሺህ በላይ ጎብኚዎች ይታደሙበታል ተብሎ በሚጠበቀው አውደርዕይ ላይ ተሳታፊዎች ምርታቸውና አገልግሎታቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከበረው የጥራት ቀን የጥራት መስፈርት አሟልተው የሚያመርቱና አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አመልክቷል።

በጥራት ዙርያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ድርጅቶችና ባለሙያዎች እውቅና የመስጠት ሁነት እንደሚካሄድም ተጠቅሷል።

የዓለም የጥራት ሳምንት በተባበሩት መንግስታት የ1990ዎቹን የጋራ ስምምነት መሰረት በማድረግ ህዳር በገባ በሁለተኛው ሳምንት በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል።

ሐመረ ፍሬው

ህዳር 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *