በጋምቤላ ክልል በከፍተኛ መጠን የስደተኛ ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ ተገለፀ

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ደቡብ ሱዳናውያን ናቸዉ ተብሏል።

ይህም የተገለፀዉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስደተኞች እና ተመላሽ አገልግሎት ጋር በተያያዙ የ2018 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ነዉ።

በግምገማዉ ወቅት 41 በመቶ የሚሆኑት ከደቡብ ሱዳን የመጡ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ 34 ሀገራት የመጡ ስደተኞችን ተቀብላ አስተናግዳለች ተብሏል።

ስደተኞቹም ተቀበለዉ በማስተናገድ ላይ  ከሚገኙት ክልሎች መካከል ትልቁን ቁጥር የያዘዉ የ ጋምቤላ ክልል መሆኑንና ይህም ከ 4 መቶ ሺ በላይ  ስደተኞችን እያስተናገደ እንደሆነና በየጊዜዉ የስደተኞች ቁጥር በክልሉ  እየጨመረ የመጣበት ሁኔታ እንዳለ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመለሾች አገልግሎት በሰባት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና መቀሌን ጨምሮ ወደ 70 ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች ይገኛሉ ብሏል።

እንደ ሀገር ስደተኞችን የማብዛት ፍላጎት አለመኖሩን የገለፁት የአገልግሎቱ  ዳይሬክተር ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን  በሀገር ውስጥ የድንበርም ሆነ የአየር መንገድ የሚመጡ ዜጎችን ሁሉ እንደስደተኛ መቀበል እንደማይቻል ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ያሉ ዜጎችን ሁሉ እንደ ስደተኛ ከተቀበልን ከመሰረቱ  ያሉ ችግሮች ሰፊ በመሆናቸው በርካታ ዜጋ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ከሀገር ደህንነት እና የፀጥታ ስጋት እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ህዳር 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *