የፈረንሳይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሳርኮዚ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ አጸደቀ

የፈረንሳይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ በ2012 የድጋሚ ምርጫ ዘመቻቸውን ለማካሄድ ህገ-ወጥ የገንዘብ ድጋፍን እንደተጠቀሙ የተወሰነባቸውን የጥፋተኝነት ውሳኔ አጽድቋል።

ይህ ውሳኔ በሌላ የክስ መዝገብ ይግባኝ እስኪሉ ድረስ ከእስር በተለቀቁ በሁለት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ የተሰማ ለታሪካቸው እና ለዝናቸው ተጨማሪ ሽንፈት ሆኗል።

ሳርኮዚ፤ በ2007 አሸናፊ በሆኑበት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት ከሊቢያ ሚስጥራዊ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ሴራ ጠንስሰዋል በሚል ጥፋተኛ ከተባሉ በኋላ በፓሪስ ላ ሳንቴ ወህኒ ቤት ለ20 ቀናት ታስረው ቆይተዋል።

ሳርኮዚ በበኩላቸው ምንም አይነት ጥፋት አለመፈጸማቸውን በመግለጽ ክሱን አስተባብለዋል።

የሰበር ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ፥ሳርኮዚ ባልተሳካው የምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት በማጭበርበር ከመጠን በላይ ወጪ በማውጣታቸው የተላለፈባቸውን የአንድ ዓመት እስራት ግማሹ በይቅርታ የሚታለፍ ሲሆን፤ የመጨረሻ እና የማይቀየር አድርጎታል።

በፈረንሳይ ህግ መሰረት፥ይህ የእስራት ቅጣት በእግር ላይ በሚታሰር የኤሌክትሮኒክስ መቆጣጠሪያ መሳሪያ ወይም በዳኞች በሚወሰኑ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ክትትል እየተደረገበት በቤት ውስጥ ሊፈጸም ይችላል ሲል የዘገበዉ አፍሪካ ኒዉስ ነዉ።

ህዳር 18/2018 ዓ.ም

እስከዳር ግርማ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *