የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት የመገናኛ ብዙሃን የገንዘብ ድጋፍ ቋት (የሚዲያ ፈንድ) ለማቋቋም ሰሞኑን ውይይት ተደጓል፡፡
ይሄው የሚዲያ ፈንድ ከስራ ውጪ የሚሆኑ ጋዜጠኞችንም ይታደጋል ተብሏል፡፡
እንዲቋቋም ሃሳብ የቀረበበት የሚዲያ ፈንድ ለግልና ለህዝብ ሚዲያ ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግና ከመዘጋት የሚታደግ ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በርካታ የሚዲያ ተቋማት በፋይናስ ችግር በህመት ዋጋ ፤ በሳተላይት ክፍያ ወድነትና የሰራተኞች ደሞዝን ጨምሮ የአስተዳደር ወጪ መናር ሳቢያ ዘላቂነታቸው ስጋት እያጋጠመው እንደሆነ የኢትዮጽያ መገናኛ ብዙሃን ም/ቤት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ታምራት ኃይሉባቀረቡት ጥናት ተመላክቷል፡፡
የፈንዱ መቋቋም ሚዲያዎቹ የሚያጋጥማቸውን የገንዘብ ቀውስ እንዲቋቋሙት ለመርዳትና በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ገለልተኛ የሚዲያ ድምጽ ቀጣይነትን እንዳይቋረጥ ለማረጋገጥ መሆኑ አቶ ታምራት አብራርተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈ የሚዲያዎችን ተቋማዊነት ነጻነት እና ብዝሃነትን ለማረጋገጥ ያግዛል ሲሉ አክለዋል፡፡
ጥናቱ የሚዲያ ፈንድ በመገናኛ ብዙሃን ም/ቤት በማቋቋም መንግስት በአስቸጋሪ ጊዜ ሚዲያዎችን የሚደግፍበትን አቅጣጫ አመላክቷል፡፡
የፈንዱ የፋይናስ ምንጮች መንግስት፤አለም ዓቀፍ ለጋሾች፤የግሉ ዘርፍን ጨምሮ ሌሎች የገቢ ማስገኛ መንገዶችን መከተል እንደሚቻልም ተመላክቷል፡፡
ም/ቤቱ በየሁለት ሳምንቱ በተከታታይ በሚያዘጋጀው በመገናኛ ብዙሃን ተቋማት መሀከል ባሉ ችግሮች ላይ የሚደረገው የውይይት መድረክ /የኢንተር ሚዲያ ዲያሎግ/ ላይ የምክር ቤቱ አባል በሆኑ ተቋማት መካከል አጀንዳው ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን እቅዱ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ቀርቦ በቀጣይነት ወደ ስራ የሚገባበት መንገድ እንደሚፈለግ ተገልፃል፡፡
ህዳር 18/2018 ዓ.ም
