የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ከፊታችን ሃሙስ ጀምሮ በሳምንት አንድ ቀን መመልከት የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።
ጽ/ቤቱ ከገቢዎች አገልግሎት ጋር በተያያዘ ለሚኖር ማንኛዉም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ስር መዋቀሩን አሳውቋል።
አዲስ በተዋቀረው የቅሬታ አፈታት መዋቅር የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች እንደሚመለከት ጽ/ቤቱ የገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ስር የተዘረጋዉ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ግን እንደተጠበቀ መሆኑን አስታውሷል።
ከገቢዎች ጋር የተገናኘ ቅሬታዎች ያሏቸውን ደንበኞች በሳምንት አንድ ቀን ተቀብሎ በማነጋገር መፍትሄ የሚሰጥ መሆኑን ከንቲባ ጽ/ቤት አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን ከፊታችን ሃሙስ ጀምሮ በሳምንት አንድ ቀን መመልከት የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።
ጽ/ቤቱ ከገቢዎች አገልግሎት ጋር በተያያዘ ለሚኖር ማንኛዉም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ስር መዋቀሩን አሳውቋል።
አዲስ በተዋቀረው የቅሬታ አፈታት መዋቅር የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች እንደሚመለከት ጽ/ቤቱ የገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ስር የተዘረጋዉ የቅሬታ አፈታት ስርዓት ግን እንደተጠበቀ መሆኑን አስታውሷል።
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
