አብዛኞቹ የግል ዘርፍ ተቋማት የሰራተኞቻቸውን የመደራጀት መብት ይነጥቃሉ ሲል የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን አስታወቀ

በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ አብዛኞቹ የግል ዘርፍ ተቋማት ሰራተኞች የመደራጀት መብታቸውን እንዳይጠቀሙ ይከለክላሉ ያሉት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ናቸዉ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ተቋሙ የተቋቋመው የሰራተኞችን መብት እና ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑን ጠቅሰው፤በግል ዘርፉ ላይ ያለው የግንዛቤ ዕጥረት እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል።

አቶ ካሳሁን እንደተናገሩት፤ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በግል መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ሰራተኞች ቅሬታ ሲያቀርቡ ወይንም ለመደራጀት ሲሞክሩ ከስራ ገበታቸው ይፈናቀላሉ ወይንም ከደረጃ ዝቅ ይደረጋሉ።

ፕሬዝዳንቱ ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን እንገኛለን ነገር ግን አሰሪዎች የሶስትዮሽ ጥምረት ለመፍጠር ፍላጎት የላቸውም ብለዋል፡፡

ነገርግን ይህ ሁኔታ በሁሉም የግል ተቋማት የሚስተዋል ችግር አለመሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሀና ሰይፉ

ህዳር 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *