20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በሃገር አቀፍ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር 0ቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል፡፡
ከሕዳር 25/2018 ጀምሮ በተለያዩ ስያሜዎች እየተከበረ የቆየው 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዛሬው ዕለትም “የኢትዮጵያውያን ቀን” በሚል ስያሜ በአቢዬ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስቴዲዬም እየተከበረ ይገኛል፡፡
በበአሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አፈ ጉባዔዎች እና ከንቲባዎች አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ሃደ ሲንቄዎችና ሌሎች የበዓሉ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡
ህዳር 29/2018 ዓ.ም
