በኢትዮጵያ 51 በመቶ የሚሆኑት የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ሴቶች ናቸዉ ተባለ

በሀገራችን የጤና መድህን አገልግሎት ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙት ሴቶች መሆናቸዉን ጥናት አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የአገልግሎት ሰጭዎች ጥራት ማረጋገጥ መሪ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፈለጉሽ ብርሀኔ፤ የሴቶች ተጠቃሚነት ከፍ እንዳለ ይገልፃሉ።

ስራ አስፈፃሚዋ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፤ በጤና ተቋማት ተጠቃሚዎች በሚገኘዉ ዳታ መሠረት ሴቶች 51 በመቶ ተጠቃሚ እንደሆኑና ወንዶች ደግሞ 49 በመቶ ተጠቃሚ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

በጤና ተቋማት ላይ የጤና መድህን አገልግሎት የሴቶች ተጠቃሚነት ከወንዶች ከፍ ያለበትን ምክንያት ሲያስቀምጡም አብዛኞቹ ሴቶች የህክምና ወጪን የትዳር አጋሮቻቸዉን እንዲሸፍኑ የሚጠበቁ እንደነበር ይገልፃሉ።

በጤና አጠቃቀም ሪፖርት ላይ እንደተገኘው ዉጤት አሁን ሴቶቹ በማንኛውም ጊዜ ህክምና ለመዉሰድ ወደ ጤና ተቋማት እንደሚሄዱ ወ/ሮ ፈለጉሽ ነግረዉናል።

የጤና መድህን አገልግሎቱ በአጠቃላይ ከ63 ሚሊየን በላይ ዜጎችን የጤና መድህን ሽፋን ስር ማድረስ ችሏል፤ ይህም 13.68 ሚሊየን የሚሆኑ እማወራዎችንና አባወራዎችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ህዳር 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *