ከታህሳስ 3 -6 ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ይካሄዳል ተባለ።

የክትባት ዘመቻው በመላው የሀገራችን ክፍል እንደሚካሄድ እና ከ25 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን ተደራሽ እንደሚያደርግ  የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ዘመቻ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ክትባቱን ከዚህ በፋት የወሰዱም ያልአልወሰዱም ህፃናት የሚከተቡት መሆኑ  ተገልጿል።

የፖሊዮ ክትባቱ  ቤት ለቤት  የሚሰጥ ሲሆን እስካሁን ያልተከተቡ እና ክትባት ጀምረው ያቋረጡ ህፃናትን የመለየት ስራም ተያይዞ የሚሰራበት ነው ተብሏል።

እንዲሁም ቤት ለቤት የሚደረገው የክትባት ዘመቻ ሌላ የጤና ችግር ያለባቸውን ህፃናት ለመለየት እና ወላጆችንም ስለ ክትባት ለማስተማር እንደሚያስችል  ተነስቷል።

ይህ ዘመቻ የመጀመሪያው ዙር በአፍ፤ በጠብታ የሚሰጥ ክትባት  ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚሰጥ ተጠቅሷል።

የክትባት ዘመቻውን  በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ በበቂ ሁኔታ ግብአትን የሟሟላት ስራዎች ሲደረጉ መቆየታቸው ተገልጿል ።

ሐመረ ፍሬው

ህዳር 30/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *