የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ዘርፉን ዲጂታል ለማድረግ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር የማጣጣም ስራ በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል።
ሆኖም ሁሉም የባንክ ደንበኞች ያላቸውን የባንክ ሂሳብ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያቸው ጋር ማስተሳሰር ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።
ደንበኞች ይህንን ሂደት እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ማጠናቀቅ እንዳለባቸውም ተገልጿል።
አፈፃፀሙ ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፎች በአካል በመሄድ ወይም ባንኮች በሚያዘጋጁት ዲጂታል አማራጭ (App/USSD) በመጠቀም የፋይዳ መታወቂያ ቁጥራቸውን (16ቱ አሃዝ) ማቅረብ ይችላሉ ነው የተባለው።
የፋይዳ መታወቂያ ለሌላቸው ደንበኞች ቅድሚያ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የፋይዳ ምዝገባ ጣቢያ በመሄድ መመዝገብ ግዴታ መሆኑም ተጠቅሷል።
ይህ አሰራር የማንነት ስርቆትን ለመከላከል፣ የደንበኞችን ደህንነት ለመጠበቅ እና በአንድ መታወቂያ ብዙ ሂሳቦችን በቀላሉ ለማስተዳደር ይረዳል ተብሏል ።
በተያያዘም ሁሉም ባንኮች ይህንን አገልግሎት ለመስጠት “VeriFayda 2” ወደ ተሰኘው ዘመናዊ የኢ-ኬዋይሲ (eKYC) ሲስተም ሙሉ ለሙሉ እንዲሸጋገሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ልዑል ወልዴ
ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም
