በኢትዮጵያ ለአጥንት ስብራት እና ለአካል ጉዳት ከሚዳርጉ ምክንያቶች ውስጥ የትራፊክ አደጋ ቀዳሚውን ስፍራ መያዙ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የአጥንት እና መገጣጠሚያ ሀኪሞች ማህበር ፀሐፊ ዶ/ር ንጉሱ ገ/ዮሐንስ፤ ጉዳቶችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመመዝገብ የሚያስችል ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጥንትና የሰውነት ጉዳት እየደረሰ የሚገኘው በተሽከርካሪዎች በተለይም በሞተር ሳይክሎች እና በጋሪዎች በሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎች መሆኑን ገልፀዋል።

ይህንን ችግር ለመለየትና መፍትሄ ለመስጠት እንዲቻልም በሀዋሳ የሙከራ ጊዜውን ያጠናቀቀ የአደጋ መዝገብ ስርዓት እየተዘረጋ መሆኑን ነግረውናል።

ይህ ስርዓት አደጋዎች እንዴት እና የት አካባቢ በብዛት እንደሚከሰቱ ለማወቅ የሚያስችል መረጃ እንደሌለ በመታመኑ የተጀመረ ጥናት መሆኑን አንስተዋል።

አብዛኛው ህብረተሰብ ወደ ወጌሻ የመሄድ ልምድ ስላለው ባህላዊውን የአጥንት ህክምና ከዘመናዊው ጋር ማስተሳሰር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መስራት እንደሚገባም ነው የገለፁት።

ይህም ወጌሻዎች መሰረታዊ ስልጠና አግኝተው ከአቅማቸው በላይ የሆነውን ጉዳት ወደ ጤና ተቋም ሪፈር የሚያደርጉበትን አሰራር ለመፍጠር በመታቀዱ ነው ብለዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *