ለህገወጥ ፍልሰት መበራከት ህገወጥ ደላሎች ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ ተባለ

ዜጎችን በማነሳሳት እና አታላይ አማራጮችን በማቅረብ ከሀገራቸው በህገወጥ መንገድ ተሰደው እንዲወጡ እያደረጉ እና ትልቅ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ናቸው ሲል የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፤ በኢትዮጵያ ህግ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳትፎ መገኘት እስከ ሞት የሚያደርስ ቅጣት እንደሚያስከትል ጠቅሰው፤ እስካሁን በዚህ ድርጊት ላይ ተሳትፈው የተገኙ አካላት ተገቢው የህግ እርምት እንደተወሰደባቸው አንስተዋል።

ህጋዊ መንገድ ለዜጎች ብቸኛ አማራጭ እንዲሆን፤ በመደበኛው ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚያቀኑ ሰዎች በመዳረሻቸው ይበልጥ ተከፋይ እና ደህንነታቸውም የተጠበቀ ለማድረግ በመንግስት ደረጃ እየተሰራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀዋል።

ይህን ተደራሽ ለማድረግ እና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ግንዛቤ የመፍጠር ተነሳሽነት ተወስዶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

አላስፈላጊ መስዋዕትነት ላለመክፈል፣ ሰርቶ መለወጥን አስቻይ ለማድረግ እና ከስጋት የፀዳ እንቅስቃሴ እንዲኖር ሁሉም ዜጋ ህጋዊ መንገድን እንዲጠቀም አሳስበዋል።

ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን መሠረት አድርገው በሰው ህይወት የሚነግዱ እና እንደዚህ አይነት ተግባር የሚፈፅሙ አካላት በአቅራቢያ ካሉ ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪ አቅርበዋል።

ሐመረ ፍሬው

ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *