የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ እስራኤል በኃይል በያዘችው የፍልስጤም ግዛት የዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ 19 አዳዲስ የሰፈራ መንደሮች እንዲቋቋሙ የቀረበውን ሀሳብ አጽድቋል፡፡
የፋይናንስ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች ቢሮ ይፋ እንዳደረገው የፋይናንስ ሚኒስትሩ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ ያቀረቡት ሀሳብ በካቢኔው ተቀባይነት አግኝቷል።
ይህም እስራኤል በኃይል በያዘችው የፍልስጤም ግዛት የዮርዳኖስ ወንዝ ምዕራባዊ ዳርቻ አወዛጋቢ የሆኑትን እና እስራኤል ባለፉት ሶስት ዓመታት እንዲቋቋሙ የፈቀደቻቸውን የሰፈራ መንደሮች ቁጥር ወደ 69 ከፍ ያደርጋል።
እንደ ስሞትሪች ገለጻ፤ የእስራኤል የሰፈራ መንደሮች ግንባታ መስፋፋት ፍልስጤም ራሷን የቻለች ሀገር ሆና እንዳትመሠረት ያግዛል።
ይሁንና በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ለፍልስጤም የመንግሥትነት እውቅና የሰጡ ሀገራት ቁጥር ከፍ ብሏል።
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
