የአልጄሪያ ፓርላማ አባላት የፈረንሳይን የቅኝ ግዛት አገዛዝ በወንጀል የሚፈርጅ፣ እንዲሁም ይቅርታና ካሳ የሚጠይቅ ህግ አጸደቁ

ይህ ህግ ፈረንሳይ ከ1830 እስከ 1962 ባለው የአገዛዝ ዘመን ለፈጸመቻቸው ግድያዎች፣ ስቃዮች፣ የኒውክሌር ሙከራዎች እና የሀብት ዘረፋዎችን ጨምሮ ለደረሱት በደሎች በህግ ተጠያቂ ያደርጋታል።

ይህ እርምጃ ከፈረንሳይ ጋር ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ በገባበት ወቅት የተወሰደ ሲሆን፤ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ፋይዳ አለው ተብሏል።

አልጄሪያ ለነጻነት በተደረገዉ ጦርነት ወቅት 1.5 ሚሊየን ሰዎች መሞታቸውን ስትገልጽ፤ፈረንሳውያን የታሪክ ተመራማሪዎች ግን የሟቾቹን ቁጥር 5መቶ ሺህ አካባቢ እንደሆነ ይገምታሉ።

ፈረንሳይም በአልጄሪያ ለነበራት የቅኝ ግዛት ታሪክ እስካሁን ድረስ በይፋ ይቅርታ ጠይቃ አታውቅም ያለዉ ዲ-ደብሊዉ አፍሪካ ነዉ።

እስከዳር ግርማ

ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *