ይህን አገልግሎት ይፋ ያደረገው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ነው።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ እንደገለጹት፥የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአካል ቢሮ ሳይገኙ መታወቂያቸውን ማደስና የልደት ሰርተፊኬት ማውጣት የሚችሉበት የዲጂታል ፖርታል ሥርዓት ተዘርግቷል።
በዚህ ሥርዓት መሠረት የቤት ባለቤቶች ለተከራዮቻቸው ወይም አብረዋቸው ለሚኖሩ ሰዎች በስልካቸው በሚላክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ማረጋገጫ በመስጠት የምዝገባ ሂደቱን ማከናወን እንደሚችሉ ተገልጿል።
ይህ አሠራር በወረዳ ቢሮዎች የሚታየውን ረጅም ሰልፍና እንግልት በእጅጉ እንደሚቀንስ የታመነበት መሆኑንና ነዋሪዎች መታወቂያቸውን ሲታተም ብቻ በአካል በመሄድ መረከብ እንደሚችሉ ሀላፊዉ አስታውቀዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
