ልዩ መለያ ኮድ/QR Code/ የሌለበት የማንዋል ደረሰኝ የአገልግሎት ጊዜ ታህሳስ 30/2018 ዓ/ም ይጠናቀቃል ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ይህንን በማስመልከት አስቸኳይ ያለዉን ማስታወቂያ አዉጥቷል፡፡
ልዩ መለያ ኮድ/QR Code/ የሌለበት የማንዋል ደረሰኝ የአገልግሎት ጊዜ ሊጠናቀቅ የቀሩት ጥቂት ቀናት በመሆኑ ልዩ መለያ ኮድ/QR Code/ ያለበትን ደረሰኝ እንድታሳትሙ እና ጥቅም ላይ እንድታውሉ በድጋሜ ለማሳሰብ እንወዳለን ሲል አሳዉቋል፡፡
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
